YANM

YANMYANMYANM

+1.3012546828

  • Home
  • About us
  • What we do
  • Testimonies
  • Blog
  • Contact
  • Donation
  • Our Mission
  • More
    • Home
    • About us
    • What we do
    • Testimonies
    • Blog
    • Contact
    • Donation
    • Our Mission

+1.3012546828

YANM

YANMYANMYANM
  • Home
  • About us
  • What we do
  • Testimonies
  • Blog
  • Contact
  • Donation
  • Our Mission

Daily message (የዕለቱ መልእክት)

ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። በመላው አለማት ያላችሁ የምጽአቱ አዋጅ ነጋሪ አገልግሎት የዩቲዩብ የጂኤም ኤም ቲቪ እንዲሁም የቲክቶክ ቤተሰቦቻችን እንዴት ሰነበታችሁ እንዴትስ ከረማችሁ። እግዚአብሔርን ስለሁሉም ነገር እጅግ አድርገን እናመሰግነዋለን። በየሳምንቱ ወደእናንተ የሚደርሰው የቤተክ/ን የምድር ቆይታዋን አስመልክቶ የመጠናቀቁን የማንቂያ መረጃዎችን በማሳየት ከሰማይ መለከት ይነፋል ብለን መለከት ነፊዎች ነን። አብሮነታችሁ ከእኛ ጋር የሆነ በመላው አለማት ያላችሁ እኛንም የምታነቁን ወገኖች ሁሉ እግ/ር ይባርካችሁ አሁንም ከኛ ጋር ሁኑ። በየሳምንቱ ወደ እናንተ የምናደርሰው ድንገተኛ ስለሆነው የቤተ ክ/ን መነጠቅን አስመልክቶ በመረጃ የተደገፈ ማዘጋጃንና በጉጉት እንድንጠባበቅ አስደራጊውን የዚህን ሳምንት የምጻቱ አዋጅ ነጋሪ አገልግሎት የንጥቀታዊ ማነቃቂያ ዜናችንን ይዘንላችሁ ቀርበናል። በ1ኛ ዮሐ 3፦9 ላይ “የዲያቢሎስን ስራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ”። ይለናል። ጌታ ኢየሱስ ክ/ስ ፍጹም ሰውና ፍጹም አምላክ ሆኖ ወደ ዚህ ምድር ከ2 ሺ አመታት በፊት የአለምን ሀጢአት ሊያስወግድ መርገምን ሁሉ ተሸክሞ በመስቀል ላይ በመሞትና ሞትን ድል አድርጎ በመነሳት በትንሳኤው ጉልበት የዲያቢሎስን እኩይ ስራዎች ሁሉ ፣ክፉ ጥበቦቹን ሁሉ አፈረሰበት። ሀይሉን ባዶ ከማድረግም ባሻገር እባቡንና ጊንጡን የመርገጥ ስልጣንን፣ ለቤተ ክ/ን ሰጠ። አሸንፎት ጨርሶ ድል አድርጎ ወደ አባቱ በማረግ ገባ መንፈስ ቅዱስም ወረደ የተሰጣትን ስልጣን በትክክል እንድትጠቀምበት እገዛ ሊያደርግ፣ሊመራትና ሊቀድሳት መጣላት እስካሁንም አለ። ከተሸነፈ 2 ሺህ አመታት የሞላው ዲያቢሎስ ከቤተ ክ/ን ጋር ደግሞ እየተጋደለ እስከዛሬ አለ መጋደላችን ከደምና ከስጋ ጋር አይደለምና እንደተባለው። ይሁን እንጂ ከ2 ሺ አመታት በፊት ዲያቢሎስ የተባለውን የሰይጣንን ስራ ለማፍረስ የተገለጠው ጌታ አሁንም ለ2ተኛ ጊዜ ተገልጦ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከማፍረስም አልፎ ወደ ማይወጣበት ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ይጥለዋል ይሄ የነገስታት ንጉስ መገለጥ ደርሷል። ያን ጊዜ የተነገረለት እውን ይሆናል “የወንድሞች ከሳሽ ተጥሏል” ይባላል፣ ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ ይነግሳል፣ የምድር ነገስታት ገዢም እንደተባለለት ይሆናል፣ ሁሉንም ይቆጣጠራል። ከሳሽ ከዚያ በኋላ በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ስፍራ አይኖረውም ሀሌሉያ። እንኳንስ አሁን በመጨረሻው መጨረሻ የመጣያው ጫፉ ጋር በደረስንበት ወቅት ቀርቶ ገና ጌታ ኢየሱስ በምድር 30 አመታት በስጋ አካል በኖረበት ጊዜ “ያለጊዜያችን ልታጠፋን መጣህን?” ብሎ ተናግሮ ነበር። የመጥፊያው ቀን እንደተቆረጠለት ጠንቅቆ ያውቅ ነበርና። ዘንድሮ ግን ጊዜው ደርሷል። “በታላቅ ቁጣ ወርዷልና የተባለለት የሞት ሽረት ትግሉን በአለም ህዝብ ሁሉ ላይ በመሰልጠን ሰዎችን ለራሱ ለማድረግ ትልቅ ሽሚያ ላይ ነው። ጦርነቱም አላሰራህም ከምትለው ባለስልጣኗ ቤተ ክ/ን ጋር ነው። ያኔ ድሮ ለማፍረስ የተገለጠው ኢየሱስ አሁን ደግሞ ሊደመድመው፣ ሊያጠናቅቀው ይገለጣል። ወደ መሬት የተጣለው የቀደመው እባብ የሰውን ዘር ወደ ማያገኝበት ሊወጣበት ወደ ማይችለው ጥልቅ ውስጥ አንድ ሺ አመታት ከነጭፍሮቹ ሊወረወሩና ሊዘጋባቸው ሊቆለፍባቸውም የቀረው ጥቂት ነው። ይህም በእኛው ዘመን እንደሚሆን እንገምታለን። ለዚህም ነው አለማትን ከዳር እስከዳር ማተራመሱ፣የክፋቱ ጡዘት መጨመሩ፣ በተለይም የቴክኖሎጂውን ደረጃ እየጨመረ የAI አብዮት ድረስ አምጥቶታል። ይህም በራዕይ 13 ላይ እንደተጻፈለት ለመጨረሻ እንዲያደርግ በተፈቀደለት መሰረት “. . . ትንፋሽ እንዲሰጥ ተሰጠው” የተባለው እሙን እየሆነም እየታየ ይገኛል። አለማትን ዋው ያስባለ የ AI አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አሰራር በድኖችን ህይወት እንዲኖራቸው እስከማስመሰልም ደርሷል። በዚህም ተንኮሉና ማታለሉ አዳምና ሄዋን ጋር ያደረገው ሽንገላ መጨረሻው ላይም “የዲያቢሎስ ስራ” የተባለውን ማድረግ ጀምሯል ይህም ስለተፈቀደለት ነው። ተንጠፍጥፎ የሚጨረሰው የመጨረሻው እውቀቱ ይህንኑ AIኡን ተከትሎ ቤተ ክ/ን ከተነጠቀች በኋላ አለማት ለእርሱ የሚሆኑበትን ቺፕሱን በግንባርና በእጅ ላይ የማስከተቡ ስራ ይቀጥላል። እንደ እግዚአብሔር የመሆን ናፍቆቱ ሳይወጣለት ምንም ያህል ዘመን ሳይኖር ሰባት አመታትን ከሰለጠነባቸው በኋላ ጌታ ኢየሱስ ክ/ስ የዲያቢሎስን ስራ ለማውደም ይገለጥበታል ተንጠልጥሎ ከነጭፍሮቹ ወደ ጥልቅ ይወረወራሉ። መቸስ ባለፉት ሺ አመታት እስከዛሬ የሚሸምቀውን የተንኮል ስራውን ባያፈርስበት ኖሮ አንዳችንም ባልኖርን ነበር። ምክኒያቱም የእርሱ አላማ ማረድ፣መስረቅና ማጥፋት ስለሆነ። ከጥቂት አመታት በኋላ ግን በየትኛውም አለም አንድ እንኳ ክፉ መንፈስ ሳይገኝ ሙልጭ ጥርግርግ ብለው ይገባሉ። የዚያ ጊዜ ምን አይነት አለም እንደምትኖር ለመገመት ከባድ አይደለም። ያለው የታመነ ነው ያደርገዋል። እኛ ግን እንንቃ እናነቃቃ።


Copyright © 2025 YANM - All Rights Reserved.

This website uses cookies.

We use cookies to analyze website traffic and optimize your website experience. By accepting our use of cookies, your data will be aggregated with all other user data.

DeclineAccept